👉50 ቦይንግ አውሮፕላኖችንም ትገዛለች ተብሏል
ሐምሌ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢንዶኔዥያ ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ምርቶቿ የምትከፍለው ቀረጥ ከቀድሞው 32 በመቶ ወደ 19 በመቶ ዝቅ እንዲል የሚያደርግ አዲስ የንግድ ስምምነት መደረሱን አስታወቁ።
በምላሹም ኢንዶኔዥያ 50 ቦይንግ አውሮፕላኖችን፣ 15 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው የአሜሪካ የኃይል ምርቶችን እንዲሁም 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የእርሻ ምርቶችን ከአሜሪካ ለመግዛት ተስማምታለች ነው የተባለው።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢንዶኔዥያን የንግድ ስምምነት ይፋ ያደረጉት፣ ፍትሃዊ የንግድ ልውውጥ እንዲኖር እና የአሜሪካን ከፍተኛ የንግድ ጉድለት ለመቀነስ በሚያደርጉት ሰፊ ጥረት አካል ነው ተብሏል።
ኢንዶኔዥያ ከአሜሪካ የንግድ አጋሮች መካከል አነስተኛውን ብትይዝም (በ2024 ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ንግድ የተካሄደ ሲሆን)፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ እንቅስቃሴ እያደገ መጥቷል ነው የተባለው። ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ወደ ኢንዶኔዥያ የምትልከው ምርት በ3.7 በመቶ ሲያድግ፣ ኢንዶኔዥያ ወደ አሜሪካ የምትልከው ምርት ደግሞ በ4.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፤ ይህም ወደ 18 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የንግድ ጉድለት አስከትሏል ነው የተባለው፡፡
ምላሽ ይስጡ