ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ የጥብቅና ሙያ እንደሌላው ንግድ መታየት የለበትም ሲል የፌደራል ጠበቆች ማህበር አስታውቋል፡፡ የማህበሩ አባል የህግ ባለሞያና ጠበቃ ወንድምአገኘሁ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ መሰረትም ሙያው እንደሌላው የንግድ አይነት መታየት እንደሌለበት ቢደነግግም፤ በሥራ ላይ ግን በተቃራኒው እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ማህበሩ ባለፉት ሦስት አመታት በገቢ ግብር ዙሪያ ጥናት ሲያደርግ እንደነበር የተናገሩት አቶ ወንድምአገኘሁ የጥብቅና ሙያ ከሌላው የንግድ አይነት በተለየ መልኩ ምርትና አገልግሎትን ማስተዋወቅ በንግድ ሕጉ የተከለከለ መሆኑንም ገልፀዋል። ጠበቆች በአመት ውስጥ በሚሰጡት አገልግሎት ውስጥ ከሦስት በላይ የሚሆኑ አገልግሎቶችን በነፃ እንደሚሰጡምና ረቂቁ ባለሙያው ከዘርፉ እንዲሸሽ ሊያደርገው እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይም በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትን ወክለው የተገኙት አቶ ፀደቀ ድጋፌ ረቂቅ አዋጅ በግልፅ ሳይሆን አሻሚ በሆነ መልክ ነው የተቀመጠው ብለዋል፡፡ ቲክቶክና ዩቱዩብ በገቢ ግብሩ እንዲካተቱ የተደረገው በምን አግባብ ነው ሲሉም ጠይቀዋል፤ በአንድ ግብይት እስከ 30ሺህ ብር ድረስ ብቻ የእጅ በእጅ ግብይት መፈቀዱ አሁን ላለው የገበያ ዋጋ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የህግ ባለሙያዎች ቢዝነስ በሚል እንጂ በነጋዴው ዘርፍ ላይ አለመካተታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ተወዳጅ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ ረቂቁ በተለይ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ በኢትዮጵያ ፈታኝ የሆነውን የታክስ ስወራን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ