ሐምሌ 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጀርመን ውስጥ አንድ ሐኪም 15 የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን (palliative care) ታካሚዎችን በመድኃኒት ድብልቅ በመግደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ለፍርድ መቅረቡ ተዘግቧል።
ዐቃቤ ህጎች እንደሚሉት፣ ሃኪሙ ታካሚዎቹን ከገደለ በኋላ ወንጀሉን ለመደበቅ ሲል በተጠቂዎቹ ቤቶች ውስጥ እሳት በማቀጣጠል ማስረጃዎችን ለማጥፋት ሞክሯል። ይህ ድርጊት በጀርመን ህግ አስከባሪ አካላት ዘንድ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል ነው የተባለው።
የዚህ አሰቃቂ ወንጀል ዝርዝሮች እስካሁን ሙሉ በሙሉ ይፋ ባይሆኑም፣ ክሱ በህክምናው ዓለም እና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል ነው የተባለው። ሐኪሙ ለምን ይህን ድርጊት እንደፈፀመ እና በየትኛው የህክምና ተቋም ውስጥ ይሰራ እንደነበር የሚገልጽ መረጃ እስካሁን አልተገለጸም ተብሏል።
የጀርመን የፍትህ ስርዓት በክሱ ላይ ምርመራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ማስረጃዎችን በመመርመር እና የሁለቱንም ወገኖች ክርክር በማዳመጥ ውሳኔውን ይሰጣል። የዚህ የፍርድ ሂደት ውጤት በጀርመን ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት የሚስብ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ