ሐምሌ 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከዚህ ቀደም ዲያስፖራው ማህበረሰብ በበየነ መረብ እና በሌሎች አማራጮች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳውን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ዲያስፖራ ባለበት ሀገራት በመሄድ አጀንዳቸውን እንደሚሰበሰብ መግለጹ ይታወቃል፡፡
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተንቀሳቅሶ አጀንዳ በሚሰበስብባቸው አህጉራት እና ሀገራት የኮሚሽኑን ተወካዮች ለመቀበል ቅደም ዝግጅት ማድረጉን ለጣቢያችን የተናገሩት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የዲያስፖራ ተሳትፎ ዳይሬክተር አምባሳደር አንተነህ ታሪኩ ናቸው፡፡
ሁኔታዎችን ቀድሞ ለማመቻት የዲያስፖራ ማህበረሰብ በብዛት ይኖርባቸዋል ተብሎ በተመረጡ የዓለም ሀገራት ከሚገኙ ተወካዮች እና አምባሳደሮች ጋር በድረገጽ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በየሀገራቱ ከተደራጁ የዲያስፖራ ማህበረሰቦች እና ተወካዮቻቸው አጀንዳ ለመሰብሰብ ሲያቀና አገልግሎቱ የተለያዩ ሰንሰለቶችን በመጠቀም ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ወደ ሀገራቱ የሚያቀኑ ተወካዮችን ለመቀበልና ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡
የምክክር ኮሚሽኑ የዲያስፖራውን አጀንዳ ለማሳባሰብ ከሚሄድባቸው የዓለም ክፍሎች አንዳንድ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ አሜሪካ እና አውሮፓ ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በሀገር ደረጃ ጣሊያን፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ በርካታ የዲያስፖራ ማህረሰብ ያሉባቸው ሀገራት እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡
የኢትየጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱን አጠናቅቆ የዲያስፖራው እና የትግራይ ክልል ብቻ እንደሚቀረው መግለጹ ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ