ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተለያዩ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ እንዲሁም ድጋፍ እንዲያደርጉ በመንግስት በኩል ጥሪ እንደሚከናወን ይታወቃል፡፡
የዲያስፖራው ማህበረሰብ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፉ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የገልፁት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የዲያስፖራ ተሳትፎ ዳይሬክተር አምባሳደር አንተነህ ታሪኩ ናቸው፡፡
ይህንንም ተከትሎ በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የዲያስፖራው ማህበረሰብ እንዲሳተፍ እንዲሁም ለአዲሱ አመት ጥሪ እንደሚደረግ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዲያስፖራ የተገኘበት የ2ተኛ ትውልድ የዲያስፖራ ጥሪ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተደረገ መሆኑን በማስታወስ በሌላ በኩል ደግሞ በዓላትን ተከትሎ በሚደረጉ ጥሪዎች በርካቶች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
ይህንንም ለመደገፍ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የትራንፖርት ወጪ ቅናሽ እንደሚደረግ አንስተዋል፡፡
በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ውስጥ በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉ መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩ ተገልጿል፡፡
__
ምላሽ ይስጡ