ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የTwitter ተባባሪ መስራች የሆኑት ጃክ ዶርሲ (Jack Dorsey) ኢንተርኔት ሳያስፈልገው የሚሰራ አዲስ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ “Bitchat”ን (ቢትቻት) መልቀቃቸውን አስታወቁ።
ይህ መተግበሪያ በተለይም የኢንተርኔት ግንኙነት በማይኖርባቸው ወይም ባልተረጋጉባቸው አካባቢዎች እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።
መተግበሪያው ብሉቱዝ ሜሽ ኔትወርኪንግ (Bluetooth mesh networking) በመጠቀም ኢንተርኔት ሳይኖር ይሰራል፤ከጫፍ እስከ ጫፍ ምስጠራ (End-to-End Encryption) የሆኑ ናቸው ተብሎላቸዋል፡፡ ይህም የተጠቃሚዎችን ግላዊነት እና የደህንነት ያረጋግጣል ነው የተባለው።
ይህ መተግበሪያ በተለይ በድንገተኛ አደጋ ጊዜ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ሲቋረጥ ወይም የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት ደካማ በሆነባቸው አካባቢዎች እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆን እየተነገረለት ነው።
የጃክ ዶርሲ ይህ እንቅስቃሴ ከማዕከላዊ ቁጥጥር ነፃ የሆኑ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ መንገዶችን ለመፍጠር ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሎለታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ