በጣሊያን አንድ ሰው በአውሮፕላን ሞተር ተስቦ በመግባቱ የተነሳ ሁሉም የቤርጋሞ አውሮፕላን ማረፊያ በረራዎች እንዲታገዱ ተደረገ
ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሰሜናዊ ጣሊያን የሚገኘው የቤርጋሞ ኦሪዮ አል ሴሪዮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ አንድ ሰው ወደ አውሮፕላን ሞተር ውስጥ ተስቦ እንደገባ በሚገልጽ ሪፖርት ምክንያት ሁሉንም በረራዎች ለጊዜው ማገዱ ተዘግቧል።
አደጋው የተከሰተው ትናንት ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻውን ሲሆን፣ አደጋው የተከሰተው አንድ አውሮፕላን ለመነሳት ሲዘጋጅ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት የድንገተኛ ጊዜ ቡድኖች ወደ ስፍራው የደረሱ ሲሆን፣ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተብሏል።
የበረራ እገዳው በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ እና ወደ አውሮፕላን ማረፊያው በሚጓዙ መንገደኞች ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል ፈጥሯል ነው የተባለው።
ምላሽ ይስጡ