ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እንዳስታወቀው አሁንም ድረስ ያለ ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች ስለመኖራቸው አስታውቋል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው በትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የሲስተም አድምንስትሬሽን ቡድን መሪ አቶ ሀይማኖት አዳነ በአሁኑ ሰዓት በመዲናዋ መንቀሳቀስ ለሚፈልጉ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች ፍቃድ ማውጣት እንደሚኖርባቸው እና ለዚህም ይረዳ ሰንድ ባልስልጣን መስሪያ ቤቱ መስፈርቶች ማዘጋጀቱ አስታውሰዋል፡፡
ቡድን መሪው አክለውም በሚደረገው ምልከታ በትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የሚያዙ እንዳሉ አንስተው፤በከተማዋ ሊያሽከረክሩ የሚችሉ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች የሚሰጣቸው ፍቃድን መነሻ በማድረግ መንቀሳቀስ እንደሚችሉም ነው ያስታወቁት፡፡
ቡድን መሪው በመዲናዋ ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች እንዳሉ ጠቁመው በዚህም የተወሰዱ እርምጃዎች አሉ ብለዋል፡፡ሆኖም በልዩነት ፍቃድ ሳይኖራቸው ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ሊኖሩም ይችላሉ ሲሉ አብራርተዋል፡፡ መስፈርቱን ያማሉ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች 9 ሺህ ብቻ መሆናቸን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተሰራ ዘገባም ሞተረኞች አዲስ ዲጅታል መታወቂያ እየተዘጋጀላቸው እና ምዝገባም እየተደረገ እንደሆነ የተገለጸ ቢሆንም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለጊዜው መስፈርቱን ብቻ እንደሚያውቅ ገልጿል፡፡
ምላሽ ይስጡ