ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዋናው ምክንያት ሩበን አሞሪም መልበሻ ክፍል ውስጥ ካሜራ እንዳይቀመጥ መፈለጉን ተከትሎ ነው ተብሏል።
Prime amazon የየክለቦች የውድድር ዘመን ውጣ ውረድ ሜዳ ላይ የሚታየው የቡድን እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን እግርኳስ ከማሸነፍ እና መሸነፍ የዘለለ መሆኑን ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን የቡድኖች ውጣ ውረድ ፤ የአሰልጣኝ ታክቲክ ፤ ውጤቶችን ለማግኘች የሚከፈል መስዋትነት ፤ ድል ፤ ውጤት እጦት ፤ ከፍተኛ ትኝቅንቅ ፤ ተጫዋቾች መካከል ያለው ግንኙነት ፤ ሁሉንም የሚያስዳስስ ዘጋቢ ፊልም በልዩነት የቀጣዩን የ2025/26 የውድድር ዘመን ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ያጠናጠነ ሆኖ እንዲሰራ ለዚህም አማዞን 10 ሚሊዮን ዩሮ ለዩናይትድ ለመክፈት ተነጋግረው ከስምምነት ላይ የደረሱ ቢመስሉም አሰልጣኝ አሞሪም መልበሻ ክፍሉ ውስጥ ካሜራ እንዲገባ እንደማይፈልግ ነፃነት የሚጋፋ ጉዳይ ነው በሚል ለዚህ ፈቃድ እንደማይሰጥ መናገሩን ተከትሎ ሊሰራ የነበረው ዘጋቢ ፊልም ቀርቷል።
ከዚህ በፊት Amazon “All or nothing” በሚል ርዕስ ይዞት የወጣው እና የሰሜን ለንደኑን ቡድን አርሰናል የ2021/22 የውድድር ዘመንን ከመጋረጃ ጀርባ የነበሩ ጉዳዮችን የሚዳስሰው ዘጋቢ ፊልም ሰፊ ተቀባይነት እና ተወዳጅነትን ማትረፉ አይዘነጋም።
ዩናይትድ በተለይ በአዲሱ አነስተኛ የክለቡ ድርሻ ባለቤት በሆነው እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጀመም ራትክሊፍ ስር አሻሚ እና አከራካሪ አለፍ ሲልም አወዛጋቢ ውሳኔዎች መወሰኑ ፤ ክለቡ ምንም የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ሳይኖረው የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቁ ፤ በመጪው የውድድር ዘመን ደግሞ ክለቡ ወደነበረበት ማለትም በፊት በሚታወቅበት የስኬት ጎዳና መመለስ የሚል ትልቅ ፈተና ያለበት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የክለቡ ጓዳ ጓድጓዳ የሚወጣበት ሰአት አይደለም በሚል ይሌንን ዘጋቢ ፊልም በዚህ ሰአት ለክለቡ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል በሚል ጥያቄውን ሳይቀበሉ መቅረታቸውን The athletic ዘግቧል።
ምላሽ ይስጡ