ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ መድረክ ለማካሄድ ረቡዕ ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፕሮግራም መያዙ ተገለጸ፡፡
እንዲሁም የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ የስነምግባር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ መድረክ ለማካሄድ ረቡዕ ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፕሮግራም መያዙን ምክርቤቱ ለመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በላከው መረጃ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ