ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰኝ በመጪው መስከረም ወር ላይ በሀገረ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ላይ በሚከናወነው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እንደማትሳተፍ ያሳወቀች ሲሆን አስቀድሞ ነሀሴ ወር ላይ በአውስትራሊያ በሚከናወነው የሲድኒ ማራቶን ላይ እንደምትካፈል አሳውቃለች።
ዘንድሮ 35 ሺሕ ሯጮች ይካፈሉበታል ተብሎ የሚገመተው እና በTCS ስፖንሰር አድራጊነት በሚከናወነው የሲድኒ ማራቶን ላይ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ሲፈን ሀሰን የፊት ገጽ እንደምትሆን ይጠበቃል።
አውስትራሊያ የሯጭ ሀገር ናት ፤ ዜጎቿ በተለያዩ ሩጫ ውድድሮች ላን እንደሚካፈሉ አውቃለሁ እንደ ሲድኒ አይነት ትልቅ ማራቶን ውድድር ላይ እንደምሳተፍ ስናገር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው ስትል ሲፈን ሀሰን ተናግራለች።
ሰሐፈን ሀሰን አምና በተከናወነው የፓሪስ ኦሎምፒክ በ5ሺ እና በ10ሺ ሜትር ርቀት የብር ሜዳሊያ እንዲሁም በማራቶን ርቀት የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገቧ የሚታወስ ነው።
የጃፓኑ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሲድኒ ማራቶን ከተከናወነ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው የሚከናወነው ከዛ አንፃር ለዝግጅት እና እረፍት ለመውሰድ በቂ ጊዜ ስለማይኖራት የማትሳተፍ ይሆናል።
እኤአ ከ2013 በኋላ ሲፈን ሀሰን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እንደማትሳተፍ ስታረጋግጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደርገዋል።
ምላሽ ይስጡ