ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለማችን ትልቁ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የመኪና ማጓጓዣ መርከብ “ዩዋን ሃይ ኮው” (Yuan Hai Kou) የመጀመሪያ ጉዞውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ በግሪክ ፒሬየስ ወደብ መድረሱን የቻይና ኮስኮ ሺፒንግ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ (China COSCO Shipping Corporation Limited) አስታወቀ። መርከቡ 4,000 የቻይና ተሽከርካሪዎችን ጭኖ በሰላም ደርሷል ነው የተባለው፡፡
ይህ ዘመናዊ መርከብ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የ”ዩዋን ሃይ ኮው” መምጣት በባህር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪ ውስጥ የዘላቂነት እና የቴክኖሎጂ እድገት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል ነው የተባለው።
የቻይና ኮስኮ ሺፒንግ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ ይህ መርከብ የካርበን ልቀትን በመቀነስ እና የአካባቢን ተፅእኖ በመቀነስ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጿል።
የመርከቡ የመጀመሪያ ጉዞ ስኬታማ መሆን የቻይናን በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን የቴክኖሎጂ አቅም የሚያሳይ ሲሆን፣ ለወደፊት ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን ለማስፋፋትም መንገድ ይከፍታል ተብሎለታል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ