🔰ሳይንሳዊ ግኝቶች ምን ይላሉ?
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ናሳ እና ቶሆ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት የቅርብ ጊዜ ጥናት፣ ምድር ለዘለቄታው የመኖሪያ ምቹነት እንደሌላት አስገራሚ መረጃ ይፋ አድርገዋል።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ፀሐይ እየጨመረ በሚሄደው ብርሃኗ ምክንያት በግምት በ1 ቢሊዮን ዓመታት ውስጥ የባህር ውሀዎችን በማፍላት እና የምድርን ከባቢ አየር በመግፈፍ የምድርን ህልውና ለአደጋ ያጋልጣል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች ደግሞ የከፋውን ትንበያ ይሰጣሉ። በእነዚህ ጥናቶች መሰረት፣ የምድር ኦክስጅን ቀደም ብሎም ሊጠፋ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነበር።
እርግጥ ነው፣ የሰው ልጅ ይህ እጣ ፈንታ ከመድረሱ በፊት ከምድር ላይ ላይኖር ይችላል የተባለ ሲሆን፤ሆኖም ይህ ግኝት ምድር ለሕይወት ያላት ምቹነት ጊዜያዊ መሆኑን የሚያሳይ የኮስሚክ ማስታወሻ ነው ተብሏል።
ይህ ደግሞ ለአፍታም ቢሆን ያለንን ደካማ ባዮስፌር ለመንከባከብ እና ለመጠበቅ ትልቅ ማሳሰቢያ ሊሆነን ይገባል ሲል ጥናቱ አመላክቷል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ