ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የሕይወት ፍልስፍና ላይ ያተኮረ መጽሐፍ በሴት ልጁ፣ ፀሐፊ ሜላት ኃይሌ ተጽፎ ለንባብ ሊበቃ ነው።
በ12 ምዕራፍ ተቀንብቦ 12 ፍልስፍናዎችን የሚያትተው መጽሐፉ፣ 247 የገጽ ብዛት አለው። መጽሐፉ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በብሬል ተዘጋጅቶ በነሐሴ ወር ለአንባብያን እንደሚደርስ ተገልጿል።
መጽሐፉ በቴሌ ብር፣ በዘመን ገበያ እና በአማዞን አማራጮች ለአንባብያን እንደሚደርስ በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።
መጽሐፉ የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የሕይወት ፍልስፍናንና ሥነ ልቦናዊ ጥንካሬን የሚመረምር “ዳይሴክቲንግ ኃይሌ” የተሰኘ ነው ተብሏል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ “በብቸኝነት ጀግንነት የለም፤ ብቻዬን ብሆን ይህ ስኬት አይኖረኝም ነበር” ብሏል።
በተጨማሪም መጽሐፉ ከታዋቂው ናይጄሪያዊ ጸሐፊ አባዮሚ ሮቲሚ ጋር በመሆን እንደተጻፈ ተገልጿል።
በኢቫን ሰለሺ
ምላሽ ይስጡ