ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለንጹህ የከተማ ኑሮ ዘመናዊ እርምጃ የወሰደችው የቻይናዋ ጂናን ከተማ፣ እየተካሄደ ያለውን የግንባታ ቦታ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ግዙፍ 50 ሜትር ከፍታ ያለው በአየር የሚሞላ ጉልላት (inflatable dome) ይፋ አድርጋለች።
ይህ ድርጊት በከተማ ልማት ስራዎች ወቅት የሚፈጠረውን አቧራ ለመከላከል፣ ጫጫታን ለመቀነስ እና የአየር ብክለትን ለመቆጣጠር ታስቦ ነው ተብሏል።
ግልጽ ከሆነ እና ዘላቂነት ካለው ቁሳቁስ የተሰራው እንዲሁም በአየር ግፊት የሚቆመው ይህ ዘመናዊ ጉልላት፣ የአየር ማጣሪያ (air filtration) እና የሙቀት መቆጣጠሪያ (temperature control) ስርዓቶችን ያካተተ ነው ተብሎለታል።
ይህም የግንባታ ሰራተኞችንም ሆነ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ደህንነት እና ምቾት ለመጠበቅ ያስችላል ነው የተባለው።
ከተሞች እያደጉ ሲሄዱ እና የመሠረተ ልማት ፍላጎት እየጨመረ ሲመጣ፣ ይህን የመሰሉ መፍትሄዎች በመላው ዓለም የተለመዱ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል።
ምላሽ ይስጡ