ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ትውልዱ እንዲያውቃቸው ማድረግ እንደሚገባ የትንፋሽ ውበት የዋሽንት ኮንሰርት አዘጋጅ አቶ ጣሰው ወንድም ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ይህን ታሳቢ በማድረግም በዛሬው እለት የዋሽት ኮንሰርት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ የሚዘጋጁ ኮንሰርቶች ብዙም አልተለመዱም ያሉት አዘጋጁ ባህላዊ የሀገር የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለሰዎች በሚስማማ መልኩ ማቅረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የዋሽንቱ ኮንሰርት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚዘጋጀ የገለፁት የኮንሰርቱ አዘጋጀና የዋሽንት ተጫዋቹ አቶ ጣሰው ወንድም ባለሙያዉ በጥራት የተሻለ ነገር ማቅረብ እንደሚገባዉ አክለዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ በዘርፉ የሚሰሩ ሰዎች ትኩረት በማድረግ ሰዉ ወደ ባህላዊ ሙዚቃ እንዲመለስ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።
በኮንሰርቱ በርካታ የዋሽንት ተጫዎቾች እንደሚኖሩ በማንሳት በቀጣይ ተመሳሳይ ኮንሰርቶች እንደሚካሄዱ አመላክተዋል።
የዋሽት ኮንሰርቱ በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞችና በውጭ ሀገራት ለማዘጋጀት እቅድ መኖሩን ተናግረዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
በመዲና አውሰይድ
ምላሽ ይስጡ