👉አዲሱ ግኝት በስነ ፈለክ ጥናት አለምን አስደምሟል!
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጄምስ ዌብ የጠፈር ቴሌስኮፕ (JWST) ባደረገው ታሪካዊ ምልከታ፣ በሩቅ የምትገኝ “የከሸፈ ኮከብ” ተብላ በምትጠራው ቡናማ ድንክ (brown dwarf) VHS 1256–1257 b ከባቢ አየር ውስጥ ከአሸዋ የተሰሩ ደመናዎች (sand clouds) መገኘታቸው ተረጋግጧል።
ይህ ግኝት ስለ ህዋ አካላት ያለንን እውቀት የሚቀይር ትልቅ ምዕራፍ ነው ተብሎለታል።
የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በጄምስ ዌብ የጠፈር ቴሌስኮፕ አማካኝነት በድንቅ ሁኔታ የተገኙት እነዚህ ደመናዎች የተፈጠሩት ከአሸዋ ጋር በሚመሳሰሉ የድንጋይ አምጪ ቅንጣቶች በተለይም የሲሊኬት ቅንጣቶች መሆኑን አረጋግጠዋል።
ይህች “የከሸፈች ኮከብ” የምትባለው አካል ከጁፒተር በ19 እጥፍ የምትበልጥ ብዛት ያላት ሲሆን፣ ከምድር 72 የብርሃን ዓመታት ርቃ ትገኛለች። እውነተኛ ኮከብ ለመሆን የምትበቃ ትንሽ በመሆኗ “ፕላኔት” ለማለት ደግሞ ከመጠን በላይ ግዙፍ በመሆኗ፣ በኮከቦች እና በፕላኔቶች መካከል ባለ መሃል መንገድ ላይ ትገኛለች ነው የተባለው።
ይህ ግኝት ከፀሃይ ስርዓታችን ውጪ በምትገኝ የፕላኔት-መጠን ባለው የሰማይ አካል ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ የተገኘ የድንጋይ ደመና ሲሆን፣ ስለ ቡናማ ድንክ ኮከቦች እና ስለ እንግዳ፣ እሳታማ ሰማያቶቻቸው ያለንን ግንዛቤ እንደገና እየጻፈ ነው ተብሎለታል።
ይህ ግኝት የወደፊት የስነ ፈለክ ጥናቶችን አቅጣጫ የሚመራ እና ስለ ህዋ አመሰራረት ተጨማሪ ብርሃን የሚሰጥ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ