ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ካላት እምቅ የሰው ሀይል መካከል ወጣት ክፍሉ ይገኝበታል ያለው የኢፌድሪ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል እንዳሉት ባለፉት አመታት ፎረሙ ስራዎችን በማከናወን ዛሬ ላይ 3ኛውን የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ለማዘጋጀት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አክለውም የመርሀ ግብሩ መዘጋጀት የአፍሪካን ነፃ የንግድ ቀጠናን በማሳለጥ ውስጥ ሚና እንዳለው ጠቁመው፤የመልማት እድልን በአግባቡ መጠቀም ፤ የአፍሪካን የልማት እንዲሁም ህዳሴ ማስቀጠል እንዲቻል በማድረግ ውስጥ የራሱን አስተዋፅዖ ያበረክታልም ሲሉ አንስተዋል።
ፎረሙ መዘጋጀቱ የራሱ ሚና እንዳለው ያነሱት ሚኒስትሯ በተለይም ተግዳሮቶች መፍታት የሚቻልበት ምህዳርን በመቅረፅ ውስጥ የራሱን ድርሻ ይወጣልም ብለዋል።
አያይዘውም የፖሊሲ ሀሳቦችን ማመንጨት የሚቻልበት እና ተግባራዊ የሆኑ ምላሾችን በመስጠት ውስጥም ተስፋ ሰጪ እንደሆነም አብራርተዋል።
ሚኒስትሯ በአፍሪካ ምህዳር ያሉ የስራ ፈጠራዎች በአንድ ላይ የሚተሳሰሩበት እና የአፍሪካ ምርቶች ልውውጥ የሚደረግበት ነው ሲሉም ጠቁመዋል ።
ፎረሙ በሚኖረው ቆይታም የፋይናንስ ብሎም የዲጂታል አካታችነት ተሳታፊ ናቸዉም ብለዋል። ፎረሙ ከሰኔ 30-ሃምሌ 2/2017 ቆይታውን እንደሚያደርግ ሚንስትሯ ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ