👉ከወትሮው በእጥፍ የሚበልጡ ጥርሶች ተገኙ
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሳይንሳዊ ልብወለድ የሚመስል ነገር ግን እውነተኛ ክስተት በቅርቡ ይፋ ሆኗል። ይህ ክስተት “ሃይፐርዶንቲያ” (Hyperdontia) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰዎች ከወትሮው ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ጥርሶች የሚያበቅሉበት ያልተለመደ የጤና እክል ነው ተብሏል።
ከዚህ ቀደም ከተመዘገቡ አስደናቂ ጉዳዮች መካከል አንዱ፤ አንድ ግለሰብ 81 ጥርሶች እንደነበሩት ያሳያል፤ ይህም ከተለመደው የ32 ጥርሶች ቁጥር ከእጥፍ በላይ ነው ተብሏል።
እነዚህ ተጨማሪ ጥርሶች፣ “ሱፐርኒውመራሪ ጥርሶች” (supernumerary teeth) በመባል የሚታወቁ ሲሆን፣ በአፍ ውስጥ በማንኛውም ቦታ ሊያድጉ ይችላሉ ነው የተባለው። ብዙውን ጊዜም በቀዶ ሕክምና ማስወገድን እንደሚጠይቁ ተመላክቷል።
የዚህ ሁኔታ መንስኤዎች የተለያዩ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የዘር ውርስ (genetics)፣ የእድገት መዛባቶች (developmental anomalies)፣ ወይም እንደ ጋርድነር ሲንድረም (Gardner’s syndrome) ወይም ክሌይዶክራኒያል ዲስፕላሲያ (cleidocranial dysplasia) የመሳሰሉ ሲንድረሞች እንደሚገኙበት ጥናቱ አመላክቷል።
አንዳንድ ሰዎች በእነዚህ ተጨማሪ ጥርሶች መኖራቸውን ላያውቁ ይችላሉ። ሆኖም ሌሎች ደግሞ በጥርስ መጣበብ (crowding)፣ ጥርሶች ዘግይቶ መውጣት (delayed eruptions) ወይም የመንጋጋ ህመም (jaw pain) ሊያጋጥማቸው ይችላል፤ በመሆኑም ቀደም ብሎ ማወቅ እና ምርመራ ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ