ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጥዋት ቡናዎ ከእንቅልፍ የመቀስቀሻ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ የሚወስዱት የእርጅና መከላከያ ሊሆን እንደሚችል አዲስ ጥናት አመልክቷል።
ከለንደን የንግስት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ እና ከፍራንሲስ ክሪክ ኢንስቲትዩት የተገኙ አዳዲስ የምርምር ውጤቶች እንዳመለከቱት ካፌይን (Caffeine) ኤኤምፒኬ (AMPK) የተባለ ኃይለኛ ሴሉላር መንገድን እንደሚያነቃቃ አረጋግጠዋል። ኤኤምፒኬ ሴሎች እራሳቸውን እንዲጠግኑ፣ እንዲያድጉ እና ጭንቀትን እንዲቋቋሙ የሚያግዝ ባዮሎጂያዊ የነዳጅ መለኪያ ዓይነት ነው ተብሎለታል።
በእርሾ ሴሎች ላይ ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ካፌይን የኤኤምፒኬን መቀየሪያ እንደሚያበራ ነው። ይህ ደግሞ ከእርጅና ጋር የተገናኘ ሌላ ተቆጣጣሪ የሆነውን ቶር (TOR) የተባለውን ንጥረ ነገር በቀጥታ ይቆጣጠራል ተብሏል። ይኸው የኤኤምፒኬ-ቶር መንገድ በሰው ልጆች ላይም የሚገኝ ሲሆን፣ እንደ ሜትፎርሚን (metformin) ያሉ የእድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶችም ይህንኑ መንገድ ዒላማ ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡
ምንም እንኳን ይህ ገና በቅድመ-ደረጃ ላይ ያለ ሳይንስ ቢሆንም፣ ግኝቶቹ ካፌይን ለወደፊት አዳዲስ የእርጅና መከላከያ ሕክምናዎችን ለማነሳሳት እንደሚችል ይጠቁማሉ። እስከዚያው ድረስ፣ ቡና የመጠጣት ልምድዎ ለሴሎችዎ ትንሽ የእርጅና መከላከያ ጥቅም እየሰጠ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ አመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ