menahriafm | አለማችን ላይ አሉ የሚባሉ እጅግ ምርጥ እና አጓጊ ፍልሚያዎችን በማዘጋጀት የሚታወቀው UFC አይን በማያስከድኑ ፍልሚያዎች ይዞ ትላንት ሲመለስ የሚያስቆመው የጠፋው የጆርጂያ እና ስፔን ጥምር ዜግነት ያለው ኢሊያ ቶፑሪያ የሁለት የክብደት እርከን የቀበቶ ባለቤት መሆን ችሏል።
የድብልቅ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከናቸው ተከፋፍለው የሚያከናውኑት የፍልሚያዎች አለም እንደሆነ ይታወቃል።
ታዲያ በቀላል ሚዛን የሪያል ማድሪድ ደጋፊ የሆነው እና የስፔን እና ጆርጂያ ጥምር ዜግነት ያለው ilia topuria ከብራዚላዊው ቻርልስ ኦሊቬራ ጋር ቀበቶውን የግላቸው ለማድረግ ላስ ቬጋስ ግዙፉ T-mobile arena ላይ ተገናኝተው ቶፑሪያ ቀደም ብሎ እንደተናገረው ቃሉን በተግባር በማዋል ብራዚላዊው ቻርልስ ኦሊቬራን ገና በመጀመሪያው ዙር በዝረራ በመርታት ቀበቶውን የግሉ አድርጎታል።
እንደሚታወቀው በFeather weight division ወይም በላቫ ሚዛን የክብደት እርከን ላይ የቀበቶው ባለቤት ቶፑሪያ ነበር ግን ክብደቱን ከፍ አድርጎ ወደ ቀላል ሚዛን በመምጣት ከኢስላም ማሀቼቭ ጋር ለመፋለም ነበር የታሰበው ኢስላም ደግሞ ክብደት ጨምሮ ወደ Welter weight ማቅናቱን ተከትሎ የፍልሚያው አፍቃሪያን ሲጠብቁት የነበረው ፍልሚያ ሳይሳካ ቢቀርም ከቻርልስ ኦሊቬራ የቀድሞ ሻምፒዮን ነው ድጋሜ በዚ ቀላል ሚዛን የክብደት እርከን ላይ ሻምፒዮን መሆንም ይፈልጋል ግን ህልሙ በጊዜ ተቀጭቶበታል።
ኤል ማታዶር እየተባለ የሚጠራው ቶፑሪያ የምሽቱን ፍልሚያ ጨምሮ እስካሁን ፕሮፌሽናል 17 ፍልሚያዎችን አድርጎ 17ቱንም ማሸነፍ ሲችል ሽንፈት የሚባል ነገር አጋጥሞት አያውቅም ፤ የሚያስቆመው የጠፋ የሚመስለው ቶፑሪያ በቀኝም ሆነ በግራ እጁ የሚሰነዝራቸው ቡጢኞች ከቀላል ሚዛን ክብደት ካለው ሰው ሚሰነዘር አይመስልም ፤ ለዚህም ገፈቱን የቀመሱት አሌክሳንደር ቮልክኖቭስኪ ፤ ማክስ ሆልዌይ ምስክሮች ናቸው። ምሽቱን ደግሞ ቻርልስ ኦሊቬራም ይህ እጣ ፋንታ አጋጥሞታል።
ኢሊያ ቶፑሪያ በUFC ውስጥ በሁለት የተለያዩ የክብደት እርከኖች የቀበቶ ክብርን መጎናፀፍ የቻለ 10ኛው ተፋላሚ መሆን ችሏል።
በቀጣይ ተዘርሮ ከማያውቀው እንዲሁም ከቶፑሪያ ጋር ከፍተኛ የባለአንጣነት ስሜትን ካዳበረው እንግሊዛዊው ፓዲ ፒምብሌት ጋር እንደሚፋለሙ እየተገለፀ ይገኛል።
ምላሽ ይስጡ