🛑የ15 ዓመቱ ፊሊፒናዊ ተማሪ የፈጠረው አስደናቂ ጫማ
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)”እግር ይራመዱ፣ ስልክዎን ይሙሉ፣ ዓለምን ያሸንፉ!” የ15 ዓመቱ ፊሊፒናዊ ተማሪ በእግር እየተጓዙ ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ እና ስልክዎን የሚሞሉ አስደናቂ ጫማዎችን በመፈልሰፍ የቴክኖሎጂውን ዓለም አስገርሟል። ይህ አብዮታዊ ንድፍ ዕለታዊ እርምጃዎቻችንን ወደ ግላዊ የኃይል ምንጭ የሚለውጥ ነው ተብሎለታል።
ይህ ፈጠራ መሳሪያዎችዎን ኃይል መሙላት የሚችሉበት ዘላቂ እና ተግባራዊ መንገድ እንደሚያቀርብና ቀላል እንቅስቃሴን ወደ ጠቃሚ ኃይል በመቀየር ለተንቀሳቃሽ ኃይል አቅርቦት ትልቅ ምዕራፍ ነው ተብሎለታል።
ይህ የፊሊፒናዊው ወጣት ፈጠራ እንደሚያሳየው፣ አዳዲስ ሀሳቦች እና የፈጠራ ስራዎች ዕለታዊ እንቅስቃሴዎቻችንን ወደ ጠቃሚ የኃይል ምንጮች የመቀየር አቅም አላቸው ተብሏል። ይህ ቴክኖሎጂ ወደፊት በስፋት ጥቅም ላይ ከዋለ፣ በተለይም የኤሌክትሪክ አቅርቦት ውስን በሆነባቸው አካባቢዎች እና ለቋሚ ተንቀሳቃሽነት ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ነው የተባለው።
በመላው ዓለም፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ የኃይል እጥረት አሁንም ትልቅ ፈተና ነው። እንደነዚህ ያሉ ፈጠራዎች በትንሹ የኃይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ እና የዲጂታል ክፍፍልን ለማጥበብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡
የዚህ ወጣት ተማሪ ስኬት፣ የወጣቶችን አቅም እና ለችግሮች መፍትሄ የመስጠት ብቃትን የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ በየሀገሩ ያሉ ወጣት ፈጣሪዎች በየራሳቸው ፈጠራ እንዲነሳሱ እና ለዓለም አቀፍ ችግሮች መፍትሄ እንዲያመጡ እንደሚያበረታታ እየተነገረ ነው፡፡
የዚህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ አተገባበር በከተሞች እና በገጠር አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች የሞባይል ስልክ ኃይል መሙላት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። በተለይም አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በእግር ለሚንቀሳቀስባቸው የአፍሪካ ሀገራት፣ ይህ ጫማ እጅግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
ቴክኖሎጂው ተሻሽሎ በጅምላ ምርት ከተጀመረ፣ የሞባይል ስልክ ኃይል መሙላት አገልግሎት ላይ ያለውን ጫና በመቀነስ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ምቹ ሊያደርግ ይችላል ተብሎለታል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ