ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ የአየር ጥቃቶች ጉዳት ደርሶበት በነበረው የኢራን ፎርዶው የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋም ላይ የጥገና ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሚያሳዩ አዳዲስ የሳተላይት ማስረጃዎች ይፋ ሆነዋል።
የሳተላይት ምስሎቹ እንደሚያሳዩት፣ ጥቃቱ በደረሰባቸው ዋሻዎችና የመዳረሻ መንገዶች ላይ በከባድ ማሽነሪዎች እና በሠራተኞች የጥገና እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህ ከዚህ ቀደም በእስራኤል እና በአሜሪካ ድንገተኛ የአየር ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶበታል ተብሎ ይታሰብ የነበረውን የፎርዶው ተቋም ሁኔታ በተመለከተ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
እስካሁን ድረስ የኢራን መንግሥት በጉዳዩ ላይ ይፋዊ አስተያየት አልሰጠም። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በሁኔታው ላይ በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን፣ የዚህ የጥገና ሥራ ትርጉም እና በኢራን የኒዩክሌር መርሃግብር ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ተጽዕኖ የተለያዩ ትንታኔዎች እየተሰጡ ነው።
ምላሽ ይስጡ