ሰኔ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኒው ጀርሲ ግዛት የሚገኝ አንድ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል፣ የዴላዌር ቤይን “የኒው ጀርሲ ወሽመጥ” (The Bay of New Jersey) በማለት እንዲሰየም ሀሳብ ማቅረቡን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ይህ ሀሳብ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጥቂት ወራት በፊት “የሜክሲኮ ወሽመጥን” “የአሜሪካ ወሽመጥ” (Gulf of America) ብለው እንዲሰየም የሚያዝ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ከፈረሙ በኋላ የመጣ መሆኑ ትኩረት ስቧል።
የኒው ጀርሲው የሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተር ማይክ ቴስታ የቀረበው የሕግ ረቂቅ፣ የዴላዌር ቤይ ስም ወደ “የኒው ጀርሲ ወሽመጥ” እንዲቀየር የሚጠይቅ ነው።
ይህ ሕግ ከፀደቀ፣ የኒው ጀርሲ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሁሉም ህትመቶቻቸው፣ ምልክቶቻቸው፣ ድረ-ገጾቻቸው እና ሌሎች መረጃዎች ላይ አዲሱን ስም እንዲጠቀሙ ያስገድዳል ነው የተባለው።
ይህ የዴላዌር ቤይን ስም የመቀየር ሀሳብ የመጣው፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሜክሲኮ ወሽመጥ ሰሜናዊ ክፍልን “የአሜሪካ ወሽመጥ” ብለው ለመሰየም ትዕዛዝ ከፈረሙ ከጥቂት ወራት በኋላ ነው።
ትራምፕ ይህን ትዕዛዝ የፈረሙት የካቲት 9፣ 2025 ሲሆን፣ ይህንኑ ቀን “የአሜሪካ ወሽመጥ ቀን” በማለት አውጀው ነበር።
የትራምፕ ትዕዛዝ በፌዴራል ኤጀንሲዎች ዘንድ አዲሱ ስም እንዲጸድቅ አስገድዶ የነበረ ቢሆንም፣ በግል ኩባንያዎችና የውጭ አካላት ዘንድ ተፈጻሚነት የለውም። ይሁን እንጂ፣ ይህ እርምጃ ሌሎች ግዛቶች የራሳቸውን የውሃ አካላት ስም የመቀየር ፍላጎት እንዲያሳድሩ እያነሳሳ ያለ ይመስላል ተብሎለታል።
ይርሃሳቡ ተቃዋሚ የኒው ጀርሲው የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተር ፖል ሞሪያርቲ፣ የሴናተር ቴስታን ሀሳብ “የግዛቱን ጊዜና ገንዘብ ማባከኛ አስቂኝ መንገድ ነው” ሲሉ እንዳጣጣሉት ተዘግቧል።
ምላሽ ይስጡ