ሰኔ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና ጉይዙ ግዛት ባደረሰው ከባድ ጎርፍ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። ጎርፉ ወደ ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች የተዛመተ ሲሆን፣ የሐሩር ክልል ዝናብ ከመግባቱ በፊት ከተሞችንና መንደሮችን አጥለቅልቋል።
የጉይዙ እና የጓንግዚ ግዛቶች አካባቢዎች በጎርፍ ተመተዋል። በተለይም ሜይሊን ከተማ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድታለች ሲል የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሐሙስ ዕለት ዘግበዋል። የጎርፍ ውሃው ከደህንነት ወሰን በላይ በ4 ሜትር (13 ጫማ) ከፍታ ላይ ደርሶ ነበር ነው የተባለው፡፡
በጉይዙ ግዛት የሚገኙት ሮንግጂያንግ እና ኮንግጂያንግ ከተሞች ቀድሞውንም በጎርፍ የተጠቁ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ሰፊው ክልል የመንገድ መደርመስ፣ የመሬት መንሸራተት እና የውሃ ግድቦች ሊፈራርሱ እንደሚችሉ ስጋት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
ማክሰኞ ዕለት፣ ሶስት ወንዞች የሚገናኙባት እና ወደ 300,000 የሚጠጋ ህዝብ የሚኖርባት ሮንግጂያንግ ከተማ፣ የቻይና የሜትሮሎጂ ባለሙያዎች በ50 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ሊከሰት ይችላል ያሉትን ጎርፍ አስተናግዳለች። በዚህም ቢያንስ ስድስት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በአንድ ወቅት፣ በሊዩ ወንዝ ውስጥ ያለው የውሃ ፍሰት ከአማካኙ በ80 እጥፍ በላይ እንደነበር ተገልጿል።
የቻይና መንግስት በጎርፍ የተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች የሰብአዊ እርዳታ እያደረገ ሲሆን፣ የማዳን ስራዎችም እየተከናወኑ ነው። የሐሩር ክልል ዝናቡ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨማሪ አደጋ ለመቀነስም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ