ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አዲሱ ሰሌዳ ስራ ላይ ሲውል የተሽክርካሪ ስርቆት እንደማይኖር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል። ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ አሽከርካሪነት እስካሁን የታወቀና የተደነገገ የስራ መደብ እንዳልነበረው ለምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ባቀረቡት ወቅት አስታውቀዋል።
እንደ ሀገር ከሚደርሱት የትራፊክ አደጋዎች 70 በመቶው በአሽከርካሪዎች ችግር የሚከሰት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ችግሩን ለመቀነስ ዘርፉን እንደማንኛውም ዘመናዊ ሙያ ቆጥሮ ማደራጀትና ማሰልጠን ያስፈልጋል ብለዋል።
በዚህም ስራና ክህሎትን መሰረት ያደረገ አሰራርና አዲስ ከሪኩለምም ተሰርቶ ማለቁን ጠቅሰው አሁን ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆን አዲስ የብቃት ማረጋገጫና የምዘና ስርአት በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ዶ/ር አለሙ ስሜ ተናግረዋል።
አክለውም በአዲሱ አሰራር የፋይዳ ምዝገባን ጨምሮ ሰሌዳን መቆጣጠሪያ ስርዓት በወጥነት ስለሚተገበር የተሽክርካሪ ስርቆት ይቀንሳል ብለዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ