ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማሰከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን በዛሬው ዕለት ገምግሟል። በዘንድሮው አመት ከያዛቸው እቅዶች አብዛኛዎቹን ማሳካቱንና የተሻለ አፈጻጸም ማስገኘቱን የገለጹት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ናቸው።
በዘንድሮው አመት ለ10ሺሕ 6መቶ 42 ደንብ ማስከበር ባለሙያዎች የሙያ ስልጠና መሰጠቱንና ፤ 5.8 ሚሊየን ለሚሆን ህዝብ በተለያዩ ሁኔታዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱን የገለጹት ዋና ስራ-አስኪያጁ ካለፈው አመት አንጻር በተሰራው ጠንካራ የደንብ ማስከበር ስራ መሰራቱን አንስተዋል፡፡
የህገወጥ መሬት ወረራ በ69.8 በመቶ መቀነሱንና በተለይም የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ በሌሎችም በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ውድመቶቸንንና የደንብ ጥሰቶችን በመቆጣጠርና ካቅም በላይ በሆኑት ላይ እርምጃ በመውሰድ በበጀት ዓመቱ 3 መቶ 97.6 ሚሊየን ብር ከቅጣት ለከተማው ገቢ መደረጉን ተናግረዋል ።
በተጨማሪም በበጀት አመቱ በከተማዋ ላይ ባሉ 72 የወንዝ ተፋሰሶችም ላይ በተደረገ ክትትል እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ አንስተው ፤ ከኑሮ ውድነትና ከህገወጥ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘም ሰፊ ቁጥጥርና እርምጃ መወሰዱን አመላክተዋል ።
በበጀት ዓመቱ ከቅጣት የተሰበሰበ 3 መቶ 97.6 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ