ሰኔ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ማገዶ፣ ኩበት እና ከሰልን በመጠቀም የዕለት ምግቡን እንደሚያዘጋጅ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጅነር ሱልጣን ወሊ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ጊዜ እንደሀገር ንጹህ የማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ቁጥር 10 በመቶ አይበልጥም።
በሀገሪቱ 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ማገዶ፣ ኩበት እና ከሰልን በመጠቀም የዕለት ምግቡን ያዘጋጃል ብለዋል።
በተለይ እናቶችና ህፃናት ምግብ ሲያበስሉ የሚጠቀሙት ማገዶ የሚፈጥረው ጭስ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተገናኘ ከፍተኛ የጤና ጉዳት ያመጣል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዘልማድ ለምግብ ማብሰያነት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶች ከእናቶችና ህፃናት ጤና አንፃር የሚያስከትሉት ጉዳት ሊፈተሽ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ለምግብ ማብሰያነት የሚውል ማገዶ፣ ከሰልና ኩበት የአየር ንብረት ለውጥ መንስዔ እንደሚሆን ጠቁመው፤ እንደሀገር ያለውን የደን ሽፋን እንዲቀንስም ያደርጋል ብለዋል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር “ብሔራዊ ንጹህ ማብሰያ” የተሰኘ እና ለአሥር ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ብሔራዊ የንጹህ ማብሰያ ፍኖተ ካርታ በታሰበው ልክ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ 93 ሚሊዮን ህዝብ የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ኢፕድ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ