ሰኔ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2016 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን ስር በሚገኙ 14 ቅ/ጽ/ቤቶች 304.8 ሚሊዮን በሌሎች 10መስሪያ ቤቶችና በአንድ ቅርጫፍ 5 ሚሊዮን በድምሩ 309.8 መሊዮን ብር ሳይሰበሰብ እንደቀረ ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ተናግረዋል፡፡
በ70 የፌዴራል ተቋማት እና በ7 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቻቸው ከ404 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥትን የግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዢ ተፈጽሞ መገኘቱን ዋና ኦዲተሯ ተናግረዋል፡፡
ያለአግባብ ያወጡትን ወይንም ለመንግስት ገቢ ማድረግ ሲገባቸው ሳያስገቡ የቀሩትን በድምሩ ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መልሱ ከተባሉት መካከል 5 የገቢዎች ሚኒስቴር የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች፣ 4 የጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ እንዲሁም ወልቂጤና ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ካለባቸው ገንዘብ ከ10 በመቶ ጀምሮ ተመላሽ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
መስሪያ ቤቱ ባካሄዳቸው የሂሳብ ህጋዊነት ምርመራዎች ያላግባብ ወጭ ተደርጎ የተገኘ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ እና በዛሬው የምንዛሪ ዋጋ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ከ23 ሺህ 230 ዶላር በላይ አጥፍተው የተገኙ የፌዴራል መ/ቤቶች ገንዘቡን ለመንግስት እንዲመልሱ ተጠይቀዋል ብለዋል::
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ