ሰኔ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 11 ወራት 1ሺሕ 400 የሚሆኑ በህገ ወጥ አካላት ተይዘው የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆኑ መደረጉን የከተማው ፍትህ ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጄኔ በከተማ አሁንም በህገ ወጥ መልኩ ተይዘው የሚገኙ መሬት፣ የንግድ ቦታዎች እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በ2017 ዓ/ም በህገ ወጥ መልኩ ተይዘው የነበሩ 259 የቀበሌ ቤቶች በፍርድ ቤት ክርክር ሲደረግባቸው ቆይተው በቅርቡ ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆኑ መደረጉን አመላክተዋል።
በተጨማሪም በህገ ወጥ መልኩ በወረራ የተያዙ 58 ሼዶች እና 234 ሄክታር መሬት ማስመለስ ተችሏል ብለዋል።
አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች በህገ ወጥ መልኩ ተይዘው የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መኖራቸውን በማንሳት በቀጣይ ቤቶቹን ለመንግስት ተመላሽ የማድረጉ ስራ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የከተማው ፍትህ ቢሮ ባለፉት 11 ወራት የተለያዩ የክስ መዝገቦችን በማሸነፍ በገንዘብ ወደ 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ማድረጉን ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ