ሰኔ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ በርካታ ባህላዊ ጨዋታዎች እንዳሉ ቢገለፅም ከማስተዋወቅ እና እንዲለመዱ ከማድረግ አንፃር ብዙ እንዳልተሰራበት ይገለፃል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት እና ባህላዊ ጨዋታዎቹ የራሳቸው ህግ እና ደንብ ወጥቶላቸው ወደ ስፖርታዊ ጨዋታዎች እንዲያድጉ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዘንድሮ በጅማ እየተካሄደ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ 6 የባህላዊ ስፖርቶች መካተታቸውን ለጣቢያችን የገለፁት የባህል እና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሕይወት መሃመድ ናቸው፡፡
ከዚህም ባለፈ በፌዴሬሽኑ በኩል ይህንን ልምድ ለማዳበር የምስራቅ አፍሪካ ባህላዊ ስፖርቶች ፌስቲቫል የማዘጋዘጋጀት እቅድ መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ በባህላዊ ስፖርቶች ላይ ጥናት እና ምርምር በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በምሁራን እንዲደረግ እየተሰራ መሆኑን እና እስካሁን 10 የሚሆኑ ጥናቶችን መሰብሰባቸውን አንስተዋል፡፡
እስካሁን በባህላዊ ስፖርት ዘርፍ 11 የሚሆኑ ጨዋታዎች ጥናት ተደርጎባቸው ሀገር አቀፍ ጨዋታዎች እንዲሆኑ ህግ እና ደንብ ወጥቶላቸው እንዲካሄዱ እየተደረገ እንደሚገኝ የባህል እና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሕይወት መሃመድ በመግለፅ ሌሎችም ባህላዊ ጨዋታዎች ጥናት እየተደረገ ወደ ስፖርታዊ ጨዋታዎች እንዲካተቱ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል፡፡
የባህላዊ ስፖርቶች የጨዋታ ህጎች እየተገመገሙ መሻሻል ያለባቸውን የማሻሻል ስራ የሚከናወን በመሆኑ ከምሁራን ጋር ውይይት በማድረግ በነሃሴ ወር ላይ ህጎችን የማሻሻል ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡
ለዘመናዊ ስፖርቶች መነሻ ባህላዊ ስፖርቶች በመሆናቸው ትኩረት ሰጥቶ የማስተዋወቁ ስራ በፌዴሬሽኑ በኩል እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቷ አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ