ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በንፅህና መጠበቂያ እጥረት እና በግንዛቤ ክፍተት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩ ሴት ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
ለወር አበባ ንፅህና ተደራሽ የሆነች ሀገርን በጋራ እናረጋግጥ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ በሀገሪቱ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ተደራሽ ማድረግ ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩ ተጠቅሷል።
የጤና ሚኒስቴር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ጥናት መካሄዱነ የገለጸ ሲሆን በሀገሪቱ 110 ሚሊየን ዜጎች አሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ወደ 55ሚሊየን የሚደርሱት ሴቶች መሆናቸው አስታውቋል፡፡
35 ሚሊየን የሚሆኑት ሴቶች የወር አበባ የሚያዩበት እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆን 11 በመቶ የሚሆኑት ግንዛቤው እንደሌላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በአጠቃላይ 70 በመቶ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እንደማያገኙ በጥናት ተመላክቷል፡፡ በዚህ ምክንያት በትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙ ሴቶች ቁጥር ከ32 እስከ 68 በመቶ እንደሚደርስ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል የንፅህና መጠበቂያ ዋጋ እ.ኤ.አ በ2012 17 ብር የነበረ ሲሆን በ2024 ደግሞ 79 ብር መድረሱ እና ለዋጋው መወደድ በምክንያትነት የተቀመጠውም የኑሮ ውድነት፣ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡት ላይ ታክስ መጣሉ፣ግጭት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
የወር አበባ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ግዜ በኢትዬጵያ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ተከብሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ