ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በአቃቂ ክፋለ ከተማ በእግረኞች መንገድ ላይ በኮድ 4 ተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ የተላለፈው አሽከርካሪ ከፌደራል ፖሊስ ሲቪል ኢንጌጅመንት እና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ።
ተሽከርካሪው ንብረትነቱ የመንግስት የሆነ የአቃቂ ቃሊቲ ክፋለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ-ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የሚጠቀምበት መሆኑ ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ ከነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋል 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) ብር ተቀጥቷል ።
ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፉ የመንግስት ይሁን የግል ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ ያለዩነት በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ተቋሙ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ