ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ምንም እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ ግዙፍ የነዳጅ አቅራቢ ሃገራት ላይ ውጥረት በመፈጠሩ በአቅርቦት እና ዋጋ ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድርም አሁን ላይ መንግስት የነዳጅ ታሪፍ የዋጋ ጭማሪ እንደማያደርግ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ አስታውቀዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ሊያጋጥም የሚችለው እጥረት እና የዋጋ ጭማሪ በኢኮኖሚው ላይ ችግር እንዳይፈጥር መቋቋም የሚያስችል እቅዶችን እያዘጋጁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የነዳጅ ማደያዎች ከታሪፉ ውጪ ዋጋ የመጨመር መብት የሌላቸው መሆኑን የሚገልፁት አቶ ስመኘው፣ በንግድ ቢሮው ድረ-ገፅ ላይ ባለው ዋጋ መሰረት ብቻ መገበያየት እንደሚገባ ገልጸዋል።
አለም አቀፍ ሁኔታውን በማየት ህገወጥ የነዳጅ ዝውውር እና የዋጋ ጭማሪ እንዲሁም የምርት መደበቅ ላይ የሚሳተፉ አካላት ላይ ቢሮው እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
ህብረተሰቡ አግባብነት የጎደለው ግብይት ሲያስተውል በነጻ የስልክ መስመር 8588 ላይ ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ መልዕክት አስተላልፈዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ