ሰኔ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 38ኛ መደበኛ ስብሰባውን ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በም/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
በስብሰባ አጀንዳው፤ የም/ቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 37ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያዳምጥ ለመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በላከው መረጃ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ