ሰኔ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴ ሃቪላንድ ካናዳ ሁለት DHC-6 Twin Otter Classic 300-G አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።
ይህ ግዥ አውሮፕላኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን መርከብ ውስጥ መግባቱን ያመለክታል። ስምምነቱ የተገለፀው በፓሪስ አየር ትርኢት ላይ መሆኑ ተመላክቷል።
እነዚህ አውሮፕላኖች ውሃ ላይ ማረፍና መነሳት የሚችሉ (amphibious) ማረፊያ መሳሪያዎች ተገጥመውላቸው የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ ወደሚገኙ ሩቅ አካባቢዎችና የሐይቅ ዳርቻዎች በቀላሉ ለመድረስ ያስችላል ነው የተባለው።
የ300-G ሞዴል አውሮፕላን የተሻሻለ የአጭር ርቀት መነሳትና ማረፍ (STOL) ችሎታዎች፣ ዘመናዊ የአቪዮኒክስ ሲስተሞች እና አስተማማኝ ጥንካሬ ያለው በመሆኑ፣ አስቸጋሪ በሆኑ የመሬት አቀማመጦችና ውስን መሰረተ ልማት ባለባቸው አካባቢዎች ለመስራት ተመራጭ ያደርገዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እነዚህን አውሮፕላኖች ለተሳፋሪዎች፣ ለጭነት፣ ለአየር አምቡላንስ፣ ለቻርተር በረራዎች እንዲሁም ለአውሮፕላን ማረፊያዎች የመለኪያ ስራዎች ለመጠቀም አቅዷል ነው የተባለው።
ይህ እርምጃ አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራዎችን ለማስፋፋት፣ የኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ልማትና ቱሪዝምን ለመደገፍ ካለው ስትራቴጂ ጋር የሚስማማ መሆኑ ተመላክቷል።
Twin Otter 300-G በዓለም ዙሪያ ከ600 በላይ አውሮፕላኖች ከተመረቱት ተከታታይ አውሮፕላኖች የቅርብ ጊዜው ሲሆን፣ በአስቸጋሪ አካባቢዎች ላይ ባላቸው ሁለገብነትና አፈፃፀም የታወቁ መሆናቸው ነው የተገልጸው።
Aviation24 , flight_Global ,Aero_time
ምላሽ ይስጡ