የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ንብረት የሆኑ ሁሉም የፊት መስመር መርከቦች ከባህሬን ቁልፍ ወደብ መውጣታቸውን የሳተላይት ምስሎች ማሳየታቸውን ኒውስዊክ ዘግቧል። ይህ እርምጃ ዋሽንግተን በኢራን ላይ ለሚደረግ ጥቃት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት የመጣ ነው ተብሏል።
ቢያንስ አንድ ሊቶራል ኮምባት መርከብ፣ አራት ፈንጂ ማስወገጃ መርከቦች እና ልዩ ኦፕሬሽን ደጋፊ መርከብ ኤም/ቪ ኦሽን ትሬደር በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) የኃላፊነት ክልል ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የእነዚህ መርከቦች ከባህሬን መውጣት ወደ ፋርስ ባህረ ሰላጤ፣ ሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ እና የኦማን ባህረ ሰላጤ ወደሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች መሸጋገራቸውን እንደሚያመለክት ተንታኞች ለኒውስዊክ ተናግረዋል። እነዚህ አካባቢዎች በCENTCOM የኃላፊነት ክልል ውስጥ ወሳኝ ቦታዎች ናቸው ተብሏል፡፡
ከሰኞ ጀምሮ፣ ዩኤስኤስ ኒሚትዝ ከደቡብ ቻይና ባህር ወደ መካከለኛው ምስራቅ የተዘዋወረ ሲሆን፣ በእስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት በአካባቢው የሚገኙትን የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚዎች ቁጥር ወደ ሁለት ከፍ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ