👉እሳተ ገሞራው ሲፈነዳ 6.8 ማይል ከፍታ ያለው አመድ ደመና መትፋቱ ተዘግቧል፡፡
ኢንዶኔዥያ ውስጥ የሚገኘው ሌዎቶቢ እሳተ ገሞራ (Lewotobi volcano) ትናንት በመፍንዳቱ፣ የእሳትና አመድ ደመና ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ መውጣቱን የሀገሪቱ የጂኦሎጂካል ኤጀንሲ አስታውቋል።
ፍንዳታውን ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በአስቸኳይ ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸው ታውቋል።
በምስራቅ ኑሳ ተንጋራ ግዛት (East Nusa Tenggara province) በፍሎሬስ ደሴት (Flores Island) ላይ የሚገኘው ሌዎቶቢ፣ ሌዎቶቢ ላኪ-ላኪ (Lewotobi Laki-laki) እና ሌዎቶቢ ፔረምፑዋን (Lewotobi Perempuan) የተባሉ ሁለት መንትያ ሾጣጣዎችን ያቀፈ ነው።
እሳተ ገሞራው ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ የእንቅስቃሴ መጨመር እያሳየ እንደነበር ተገልጿል። የአካባቢው ባለስልጣናት እና የድንገተኛ አደጋ ቡድኖች ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች መጠለያና እርዳታ በመስጠት ላይ መሆናቸው ታውቋል።
የእሳተ ገሞራው እንቅስቃሴ በቅርበት እየተጠና ሲሆን፣ ለአካባቢው ነዋሪዎች እና በአቅራቢያው ለሚገኙ አካባቢዎች አስፈላጊው ማስጠንቀቂያና ጥንቃቄ እየተሰጠ መሆኑን የሚዲያ ዘገባዎች አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ