👉40 የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሩሲያ ፌዴሬሽን በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ሰኞ ምሽት በሰነዘረው የአየር ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች 40 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የዩክሬን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ስታፍ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የዩክሬን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሆር ክሊሜንኮ፣ በዋና ከተማዋ ውስጥ በሚገኙ 27 የሚሆኑ የመኖሪያ ሕንፃዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን እና ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ ጥቃት እንደደረሰባቸው አረጋግጠዋል። ከሟቾቹ መካከል የ62 ዓመት አሜሪካዊ ዜጋም እንደሚገኙበት ተዘግቧል።
ጥቃቱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ክሩዝ እና ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን በመጠቀም የተፈፀመ ሲሆን፣ የአየር ወረራ ማስጠንቀቂያ ለበርካታ ሰዓታት ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል ነው የተባለው።
ይህ ጥቃት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርጋቸው ጥቃቶች ተጠናክረው በቀጠሉበት ወቅት የመጣ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
CBS_news
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ