👉አብዛኛው ቅርስ እየወጣ ያለው በኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምዝገባ፣ ጥበቃና እንክብካቤ የሥራ አፈፃፀም ኢኮኖሚያዊ እና ውጤታማነትን በተመለከተ የ2015/16 የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ በዛሬው እለት በይፋ ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱም ቋሚ ኮሚቴው ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 24 የኦዲት ግኝት ሪፖርቶችንና ጥያቄን አቅርቧል፡፡
ባለስልጣኑ ቅርሶችን በተለይም ከጥንታዊ ብራና፣ ከከበሩ ማዕድናትና ከሌሎች ቁሳቁሶች የተሰሩ ቅርሶችን ሲመዘግብ፣ ሲረከብ ክትትልና ቆጠራ ሲያከናውን የቅርሶችን ትክክለኛነትና ዕድሜ የሚያረጋግጥበት አሰራር፣ እውቀትና ቴክኖሎጂ በማሟላት ተግባራዊ አለማድረጉን የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች የቋሚ ኮሚቴው አባል ወ/ሮ ፀሃይ በቀለ በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡
ባለስልጣኑ ክልሎችና ሌሎች ቅርስን ከሚያስተዳድሩ አካላት ጋር በመተባበር ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን በመለየት በሀገር አቀፍ የቅርስ መመዝገቢያ መዝገብ መሰረት ወጥ የሆነ የቅርሶች ምዝገባ ስራ በአግባቡ እያከናወነ አለመሆኑ፣ ምዝገባው በቴክኖሎጂ አለመደገፉና አሁንም ቅርሶች ከሃገር እየወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቅርሶችን ለመጠበቅ በሚደረገዉ እንቅስቃሴም ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ከሃገር እንዳይወጡ መከላከል እንዲቻል በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አነፍናፊ ውሾች መዘጋጀታቸውን በውይይቱ መድረኩ የተናገሩት ደግሞ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ፤ ያለፈውን ዘመን ቅርስ ከመጠበቅ ባለፈ በዘመኑ ያሉ ቅርሶችንም ማዘጋጀት ላይ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ ከፍተኛ በጀት በመመደብም የቅርስ እደሳትን ሲያከናወን እንደቆየ የሚናገሩት የባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሃፍታሙ አብረሃ ቅርሶች በ8 ዘርፍ ተለይተው እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ውስን የሰው ሃይል በባለስልጣኑ መኖሩ ከፍተኛ ችግር እንደሆነ የተናገሩት መሪ ሥራ አስፈፃሚው ከሃገር የሚወጡ ቅርሶችን ለመቆጣጠር ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር እየተሰራ እንደሆነና አብዛኛው ቅርስ እየወጣ ያለው በኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵየ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የቀረበለትን ጥያቄ በተገቢ መንገድ አልመለሰም ሲሉ የምክርቤቱ አባላት የተቹት ሲሆን በተለይም ባለስልጣኑ ከፍተኛ የሆነ የህግ ማዕቀፍ ክተት እንደለበት፤ ለኦዲት ግኝት ትኩረት እንደማይሰጥ የምክር ቤቱ ሰብሳቢዎች አንስተው፤ በሃገር ውስጥ ሰስላሉ ቅርሶች ማጥናት እንደሚገባውና ለጥናት ምርምር ክፍት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ