👉የነዳጅ ዋጋ መናር:ግጭቱ በነዳጅ ገበያው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል። ኢራን በዓለም የነዳጅ አቅርቦት ላይ ትልቅ ቦታ የምትይዝ ከመሆኗም በላይ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ (Strait of Hormuz) ለመርከቦች ወሳኝ የነዳጅ ማጓጓዣ መንገድ ነው። ግጭቱ በመካሄዱ የነዳጅ አቅርቦት ሊቋረጥ ይችላል የሚል ስጋት ስለፈጠረ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር እንዳደረገው መረጃዎች እየወጡ ነው። ይህ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ግሽበትን ሊያስነሳ ይችላል።
👉የአየር ትራንስፖርት መስተጓጎል: በርካታ አገሮች፣ በተለይም የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች (ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ ሶሪያን ጨምሮ) የአየር ክልላቸውን ዘግተዋል። በተጨማሪም፣ ዋና ዋና አየር መንገዶች በክልሉ በኩል የሚያደርጓቸውን በረራዎች አቁመዋል ወይም መንገዶችን ቀይረዋል። ይህ ደግሞ የጉዞ ጊዜን ያራዝማል፣ የበረራ መዘግየቶችን ያስከትላል፣ እና የአየር መንገድ ኩባንያዎች የነዳጅ ወጪን እንደጨመረውም ተዘግቧል፡፡
👉የክልላዊ ግጭት ስጋት: በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ሰፊ ጦርነት ሊያድግ ይችላል የሚል ስጋት አለ። ይህ ደግሞ ቀድሞውንም የተወሳሰበውን የክልሉን ሁኔታ ይበልጥ እንዲባባስ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ሌሎች አገሮችም ወደ ግጭቱ ሊገቡ ይችላሉ የሚል ስጋት መፍጠሩ ነው የተመላከተው፡፡
👉ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ: የግጭቱ መባባስ የዓለምን ኢኮኖሚ ሊጎዳ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የትራንስፖርት መስተጓጎሎች በንግድ እና በአቅርቦት ሰንሰለቶች ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። በተጨማሪም፣ የገበያ መረጋጋት ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር የአክሲዮን ገበያዎች መውረድ እና ኢንቨስተሮች በጥርጣሬ ውስጥ መውደቅ ሊገጥማቸው እንደሚችል የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ፡፡
👉ሰብዓዊ ቀውስ: በጦርነቱ ምክንያት በሁለቱም ወገኖች የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ሰብዓዊ ቀውስን እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል፡፡በጦርነቱ የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል፣ ሰዎች ለመጠለል ተገደዋል፣ እንዲሁም መሠረተ ልማቶች ተጎድተዋል። ይህ ደግሞ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና ይፈጥራል ነው የተባለው፡፡
👉የኒውክሌር ድርድር መቋረጥ:የእስራኤል እና ኢራን ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ሲካሄዱ የነበሩ ድርድሮች ሊስተጓጎሉ ወይም ሊቋረጡ እንደሚችሉም እየተገለጸ ነው፡፡
በጌታሁን አስናቀ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ