የከተማ አስተዳደሩ የኪነ-ጥበብ ዘርፉን ለማሳደግ በሚደርገው አማተር የጥበብ ሰዎችን የማፍራት ስራ ውስጥ ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ባህል ቱሪዝምና ኪነ-ጥበብ ቢሮ፣ የኪነ-ጥበብ ሃብቶች ልማት መድረኮችና ሁነቶች ዝግጅት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደኑ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
ዘርፉ የተሻለ መነቃቃት እንዲታይበት ቢሮዉ በ21 የተለያዩ ዘርፎች ላይ የስልጠና መርሃ ግብር አዘጋጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ሰለሞን፣ የጥበብ አፍቃሪያን ተማሪዎች ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ የሙያው ባለቤት ለማድረግ ቢሮው በየወረዳውና ማዕከላት የሚደረጉ ውድድሮችን አሸናፊ የሚሆኑ አማተሮችን በመቀበል የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
በዚህም አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሴቶቻና ወንዶች በባህል ሙዚቃ፣ በስዕል፣ በፊልም ዝግጅት፣ በትወናና በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እንደየ ችሎታቸው በማሰልጠን የማብቃት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ሰለሞን ገልፀዋል፡፡
እስካሁን በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ካሉ ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 30 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፎች የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት እንደተቻለ ገለልፀው ከ1ሺህ በላይ አሰልጣኞች እንደሚያሰለጥኑም አመላክተዋል፡፡
ጥበብ የአንድ ሃገር መሰረት ስለሆነና ማህበረሰብን ከማህበረሰብ ህዝብን ከህዝብ የማስተሳሰር ከፍተኛ አቅም ስላለው በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ድጋፍ በማድረግ ተተኪ የጥበብ ሰዎችን ማፍራት እንደሚገባ አቶ ሰለሞን ገልፀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ