በአማራ ክልል ኤም ፖክስ (MPox) ተላላፊ ቫይረስ በሽታ በመተማ እና ባሕርዳር ከተሞች በሁለት ሰዎች ናሙና ተወስዶ መረጋገጡን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኤም ፓክስ በሽታ ምልክቶቹ በሽተኛው ከተያዘ ከ5 እስከ 21 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች የሚታዩ መሆኑ ተመላክቷል።
ምልክቶችም ከፍተኛ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጀርባ ሕመም፣ የሰውነት ዕጢ እብጠቶች፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ በሰውነት ክፍል ጎልተው የሚታዩ ሽፍታዎች ናቸው።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የተያዙት ሰዎች ቁጥር #19 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በበሽታው እስካሁን የአንድ ሰው #ህይወት አልፏል ተብሏል።
👉 #አምስት ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል ነው የተባለው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ