በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ላይ በተደረገው የሴቶች 10ሺ ሜትር የኔዋ ንብረት የአመቱ ምርጥ ሰአቷን በማስመዝገብ ጭምር ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች።
ርቀቱን ለማጠናቀቅ 30 ደቂቃ 28 ሰከንድ የፈጀባት ሲሆን የአመቱ ፈጣን ሰአት ሆኖም ተመዝግቧል። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጫልቱ ዲዳ ደግሞ 3ኛ ደረጃን አግኝታ አጠናቃለች።
የገባችበት ሰአት 30 ደቂቃ 33 ሰከንድ ሲሆን የግል ምርጥ ሰአቷ ሆኖ ተመዝግቦላታል።
በወንዶች በተደረገው የ5ሺ ሜትር ውድድር ወጣቱ ተስፈኛ አትሌት ቢኒያም መሀሪ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
12 ደቂቃ 45 ሰከንድ የገባበት ሰአት ሲሆን የግል ምርጥ ሰዓቱም ሆኖ ተመዝግቧል።
ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኩማ ግርማ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል ፤ የገባበት 12 ደቂቃ 46 ሰከንድም የግል ምርጥ ሰዓቱ ነው።
በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት አግኝቶ የነበረው አትሌት ሀጎስ ገ/ህይዎት 5ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ 8ኛ ደረጃን እንዲሁም አትሌት ብርሀኑ ባለው 12ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሌላ ርቀት በ800 ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ኬንያዊው አትሌት ኢማኑኤል ዋንዮንዪ 1 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ስፔናዊው መሀመድ አቱዊ እና አልጄሪያዊው ጃሜል ሴድጃቲ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ምላሽ ይስጡ