የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ በ2003 ዓ/ም መጋቢት 24 ከተጣለ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች የገቢ ማሰባሰቢያ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የዘንድሮ ዓመት የግድቡ ግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ እንደመሆኑ በተለያዩ መንገዶች የሚደረጉ የገቢ ማሰባሰብ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ለጣቢያችን የገለፁት የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ግንኙነት እና የኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ዳንኤል ናቸው፡፡
የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደቱን በ8100፣ በቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ፣ በተለያዩ መተግበሪያዎች እና በሌሎችም አማራጮች እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደቱን አጠናክሮ እየሰራበት እንደሚገኝ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮ በጀት ዓመት ሊሰበሰብ ከታቀደው 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እስካሁን 1 ነጥብ 25 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን በመጥቀስ በ14 ዓመት ውስጥም ከ23 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቀዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት 8100ን እና የቦንድ ግዢን በፍተኛ ሁኔታ ማስተዋወቅ መቻሉን በመጥቀስ አሁን ላይ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮችን በመፍጠር እየሰራ መሆኑን አቶ ሰለሞን ገልፀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ