በታሪክ ረጅም ሰአት የፈጀው የሮላንድ ጌሮስ የፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ቴኒስ የፍፃሜ ውድድር በስፔናዊው ተስፈኛ የሜዳ ቴኒስ ተወዳዳሪ ካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ከራፋኤል ናዳል በኋላ ስፔን አገኘችው የሚባለው ይህ አስደናቂ አቅም ያለው የሜዳ ቴኒስ ተወዳዳሪ ሁሌም በግራንድ ስላም ትራክ የፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ አጀማመሩ ደካማ ነው ግን ከኋላ እየተነሳ ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ከአንድም ሁለቴ ታይቷል።
በፈረንሳይ ቀዩ አፈር ላይ የሚደረገው ብቸኛው አመታዊ የሮላንድ ጌሮስ የሜዳ ኦፕን ቴኒስ ውድድር ላይ ድራማዊ በሆነ መልኩ ወደ ጨዋታው በመመለስ የአለም ቁጥር 1ዱን ጣልያናዊው ያኒክ ሲነርን በማሸነፍ ትልቅ ታሪክ መስራት ችሏል።
የመጀመሪያ ሁለት ሰርቦችን እንዲሁም ዙሮቹን 6-4 እና 7-6 በመሸነፍ 2-0 እየተመራ ነበር ፤ ቀጣዮቹን 3 ዙሮች ግን 7-6 ፤ 7-6 ፤ 10-2 በድምሩ 3-2 በማሸነፍ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።
አልካራዝ ከዚ በፊት በፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ባሳለፍነው አመት አሌክሳንደር ዝቬሬዝን በእንዲሁም በ2023 በእንግሊዝ ዌምብልደን ኖቫክ ጆኮቪችን ከኋላ ተነስቶ በመርታት አሸናፊ መሆን የቻለበት አጋጣሚ መፈጠሩ የሚቻወስ ሲሎን አሁን ለ3ኛ ጊዜ በዚሁ መንገድ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጠዋል። በማህበራዊ ትስስር ገጹ እስካሁን ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኗል።
አውቄው አይደለም የፈዘዘ ጅማሮ ማሳየው ያለው አልካራዝ ግን ሁሌም በየትኛውም ሰአት ብመራም እደርሳለሁ የሚለው እምነቴ አሸናፊ ያደርገኛል ፤ ትክክለኛ ሻምፒዮኖች የሚለዩት በዚህ አጋጣሚዎች ላይ ነው ሲልም ተደምጧል።
የ22 አመቱ ስፔናዊ በዚህ እድሜው 5ኛ ግራንድ ስላም ክብሩን የተጎናፀፈ ሲሆን ወደ 2.8 ሚሊዮን ዶላር ወደ ካዝናው የሚያስገባ ይሆናል።
የአለም ቁጥር 1ዱ ያኒክ ሲነር በግራንድ ስላም የፍፃሜ ጨዋታ ሽንፈት ሲያጋጥመው ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኖም ተመዝግቧል።
የሁለቱ የቴኒስ ተወዳዳሪዎች የፍፃሜ ጨዋታ 5 ሰአት ከ29 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን በታሪክ ረጅሙን ሰአት የፈጀ በፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ጨዋታም ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚያ ውጪ ይህ ግራንድ ስላም በፍፃሜው ሁለቱም ተወዳዳሪዎች እኤአ ፈረንጆቹ ሚሊኒየም በኋላ የተወለዱ እና ከ25 አመት በታች የሆኑ ተወዳዳሪዎችን በፍፃሜው ሲያገናኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደርገዋል።
እንኳን ደስ አለህ ፣ ይገባሀል ግን የተሸነፍኩበት መንገድ በጣም ሚያስቆጭ ስለሆነ ጥሩ እንቅልፍ አገኛለሁ ብዬ አልገምትም ሲል 1.4 ሚሊዮን ዶላር ወደ ካዝናው ያስገባው ጣልያናዊው የአለም ቁጥር 1ዱ ያኒክ ሲነር ሀሳቡን ሰጥቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ