ሁለቱ አትሌቶቾ በተለያዩ ጊዜያቶች ለግል ክብርም ፤ እንዲሁም የሀገራቸውን ባንደመራ ከፍ አድርገው ለማውለብለብ በሚደረጉ ትልቅ የውድድር መድረኮች ላይ በተደጋጋሚ መገናኘታቸው ይታወቃል።
ታዲያ ነገ በጣልያን ዋና ከተማ ሮም ከተማ ላይ በሚከናወነው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ፍጥቻቸው እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።
የወቅቱ የ5000 ሜትር ሪከርድ ባለቤቷ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዴፍ ፀጋዬ ከኦሎምፒክ ሻምፓዮኗ ቢያትሪስ ቼቤት ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ ትኩረትን ስቧል።
የወቅቱ ምርጥ አትሌት በመባል በአለም አትሌቲክስ የተመረጠችው ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼቤት ሞሮኮ ራባት ላይ በ3000 ሜትር 8:11 በመግባት የአፍሪካን ሪከርድ በመያዝ እንዲሁም የአለማችን ሁለተኛውን ፈጣን ሰአት ማስመዝገቧ የሚታወስ ነው።
እንዲሁም ባለፈው ወር በቻይና ዢያመን ከተማ ላይ በ5000 ሜትር የነገ ተፎካካሪዋን አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬን በ1 ሰከንድ በመብለጥ ውድድሯን በቀዳሚነት ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
ግን ጉዳፍ ፀጋዬ በዳይመንድ ሊግ ቢያትሪስን ለመጨረሻ ጊዜ የረታቻት ብቸኛዋ አትሌት ናት እሱም ከሁለት አመት በፊት ኢውጂን ኦሪገር ላይ በተከናወነው ውድድር 14 ደቂቃ ከ92 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የወቅቱ የአለም ሪከርድን በእጃ ስታስገባ ቢያትሪስን በመርታት እና አትሌቷን አስከትላ ውድድሯን ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
ከዛ ውጪ የሁለት ጊዜ የቤት ውስጥ ውድድርን በበላይነት ያጠናቀቀችው ፍረወይን ሀይሉም ውድድሩን እንደምትካፈል ለማወቅ ተችሏል።
በ1500 ሜትር ኢትዮጵያዊያኑ ብርቄ ሀየሎም እና ሂሩት መሸሻ የሚሳተፉ ሲሆን ከኬንያዊቷ ሱሳን ኢጆሬ እና ከአየርላንዳዊቷ የአውሮፓ የ3000 ሜትር ሻምፒዮን የሆነችው ሳራ ሄይሊ ጋር የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል።
ምላሽ ይስጡ