የመመሪያው መፅደቅ በዘርፉ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመሸፈን አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ መመሪያው ግንቦት 26/2017 ዓ.ም እንደፀደቀ ገልፀው በኢትዬጵያ በመድሃኒት አቅርቦት በኩል ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ ለመስራት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡
መመሪያው መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎቱ የሃገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት፣ የህክምና መሳሪያዎች ላይ የሚስተዋለውን ክፍተትን ለመሙላት ያለመ ስለሆነ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ መሰራቱ ከመድሃኒት እስከ ህክምና መሳሪያ ድረስ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እንደሚያግዝ ገልፀዋል።
ከሶስት አመታት በፊት የሃገር ውስጥ መድሃኒት አምራቾች ቁጥር ከ8 ወደ 37 ማሳደግ እንደተቻለው ሁሉ ከውጭ ሃገር የሚመጣውን መድሃኒትና የህክምና መሳሪያ እንደ አማራጭ በመውሰድ ለሃገር ውስጥ ምርት ቅድሚያ ተሰጦ እንደሚሰራም ዶ/ር አብዱልቃድር ተናግረዋል።
ለክልሎች የመድሃኒት አቅርቦትን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ በማጓጓዝ ሂደትና ከማሰራጨት አኳያ ክፍተት እንዳለ የገለፁት ዶ/ር አብዱልቃድር፣ ይህንን ችግር ለመፍታትም የሃገር ውስጥ ምርትን ማበረታታት እንደሚገባ አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ