በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥቅም የላቸውም ተብሎ የሚጣሉ ወረቀት እና ካርቶኖችን ለስራ እድል ፈጠራ እንዲውሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አንዲ ማማ ድርጅት አስታውቋል። በተለይም በመዲናዋ አካባቢን ፅዱ ከማድረግ ጋር እየተሰራ ላለው ስራ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።
በዚህ ስራ አማካኝነትም ለበርካታ እናቶች እና ወጣት ሴቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን የአንዲ ማማ ዋና ስራ አስኪያጅ መቅደስ ተሾመ ገልፀዋል።
በእነዚህ ወረቀት የተሰሩ የተለያዩ ምርቶችን ለሆቴሎች እና ተቋማት በሽያጭ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
በዛሬው እለትም ለ4ኛ ግዜ አመታዊ ክብረበዓሉን ድርጅቱን ከሚደግፉ የተለያዩ አካላት ጋር በመሆን አክብሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ