የክረምት ወቅት ሲቃረብ የቀይ ሽንኩርት ምርት መቀነስ እና መወደድ በከተማዋ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ አመራሮች ግብረ-ሃይል በማቋቋም በሶስት ክልሎች በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ትስስር ለመፍጠር ፍለጋ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ነው ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታዉቋል።
ከሰሞኑን በመዲናዋ በቀይ ሽንኩር ምርት አቅርቦት ላይ የታየዉን የዋጋ መጨመረ እና የምርት እጥረት ለመፈታት ከፍተኛ የሆነ የበልግ እና የክረምት ዝናብ የማያስተናግዱ ቦታዎችን በመምረጥ ምርት አቅራቢዎችን ፍለጋ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ እና ግብይት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መከታ አዳፍሬ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ ባነጋገርናቸው ወቅት በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ የሚገኙ መሆኑን የነገሩን ሲሆን ከከፍተኝ አመራሮች ጋር የመግባቢያ እና የንግድ ትስስር ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ሌሎችን ምርቶችን ከቀይ ሽንኩርት ጎን ለጎን ማፈላለጉ በአፋር ፣በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በሶማሌ ክልሎች ላይ ከንግድ ቢሮው በተውጣቱ የባለሙያ እና የአመራር ቡድኖች አማካኝነት እየተካሄደ እንደሚገኝ አክለዋል ገልጸዋል።
የክረምት መዳረሻ ላይ የግብርና ምርቶች እጥረት ስጋት ለመቅረፍ የምርት ማፈላለጉ ዘመቻ በስኬታማነት እንደሚጠናቀቅ ብሎም የምርት እጥረት ችግር በመዲናዋ ላይ እንደሚፈታ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
መናኸሪያ ሬዲዮ ከቀናት በፊት በመዲናዋ የሚታየዉን የሽንኩርት ምርት እጥረት እና የዋጋ መናር ካደረገዉ ቅኝት መነሻነት ቢሮዉ ምን ምላሽ አለዉ የሚለዉን የጠየቀ ሲሆን የሽንኩርት ዋጋ የሚያስጨምር ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ እና ጉዳዩን የመከታተል ስራ እንደሚሰራ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ